
Annynomus Spokane, Wa
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በሚያዝያ 21 ቀን ለአባታችን ያደረገችለት ፈውስ
በሚያዝያ 21 ቀን ከሌሊቱ 4:30 am አካባቢ አባታችን ጀርባውን አመመውና ጋደም እንዳለ ትንፋሽ እያጠረው መጣ እና ወዲያው የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ፀበል አምጥተን ስንረጭበት ትንፋሹ ወዲያው ተመለሰ እና የእርዳታ ጥሪን በሰአቱ ደውለን ስለነበር ሲመጡ ቶሎ ብለው ተገቢውን ክትትል ካደረጉለት ቡሃላ ሆስፒታል ይዘውት ሄዱ:: ሆስፒታል ገብቶ እስከ 3 ቀን ህክምናውን ሲከታተል እኛም ቤተሰቦቹ በፀሎት እግዚአብሔርን እየለመንን ቆይተን በ3 ተኛው ቀን ምንም አይነት የጤና እክል ሳይገጥመው ድኗል ::
ይህን ድንቅ ነገር ላደረገችልን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ክብርና ምስጋና ይገባታል !!! ምልጃዋና
ምህረቷን ከሁላችን ሕዝበ ክርስትያን ጋር ይሁን አሜን!!
Our Lady, the Holy Virgin Mary, graciously performed a healing for our father on April 21st.
In the early morning, around 4:30 AM, our father came to us suffering from severe back pain and shortness of breath. We immediately brought the Holy Virgin Mary’s tsebel and sprinkled it upon him, and at once, his breathing was restored.
At the same time, we had called for medical assistance, and he was quickly taken to the hospital, where he received proper care. He remained hospitalized and under treatment for three days.
Throughout this time, we, his family, prayed earnestly to God. By the third day, he was completely healed, with no remaining health issues.
Glory and thanks be to our Lady, the Holy Virgin Mary, for this wonderful miracle she has done for us! May her intercession and mercy be with all Christians. Amen.